በማዕከላዊ ኢት/ያ ክልል በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስ/ር/ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ ጽህፈት መሣሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ ለጽህፈት መሣሪያ ግዥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢት/ያ ክልል በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስ/ር/ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ ጽህፈት መሣሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
ስለዚህ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
- ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- VAT ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት ያለው
- ዕቃ አቅራቢነት ሠርተፍኬት ያለው
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ 200 ብር በጀ/ከ/አስ/ር ገ/ጽ/ቤት በመክፈል መግዛት የሚቻል ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 በፊደልም አስር ሺ ብር በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (cpo) የሚጠበቅባቸውን የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ብቻ በመሙላት ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታው እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት የሚያበቃ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን የአንዱን ዕቃ ዓይነት ነጠላ ዋጋ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስረጃዎቻችሁን በፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚቻል ሆኖ በጀጁራ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይሆናል ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ መቅረቱ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡ ዕቃውን በሀዲያ ዞን በጃጁራ ከ/አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ ሆኖ የጨረታ ዝርዝር መረጃ የሚሞላበት ፎርማት ኮፒ ከቢሮ ቁጥር 09 ወይም ከግ/ን/አስ/ር ዋና ሥራ ሂደት እንድትወስዱ እናስታውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሀዲያ ዞን የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
