Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0221118429
  • Website
  • Deadline05 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-01-05 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Stationery Materials

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው (የህንጻ መሳሪያ) ፌሮ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 10/2018 .

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው (የህንጻ መሳሪያ) ፌሮ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦከሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የፌሮዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
  3. በጨረታው ሽያጭ የፌሮው ብረት አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
  4. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ምድብ የፌሮ ብረት የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ... በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  5. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት የፌሮ ብረቶች በአዋሳ ///ቤት የውርስ መጋዘን አስተዳዳር የስራ ሂደት ማዕከላዊ መጋዘን ጊቢ ውስጥ ስለሚገኙ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 400 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታስብላቸው ሲሆን፣ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 / ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ የፌሮ ብረቶቹን መረከብ ይኖርባቸዋል።
  8. ከላይ በተ/ 7 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ፌሮው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  9. ለጨረታ የቀረቡት የፌሮ ብረቶች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
  10. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09- 05-11-55–11/ 011-666-88–28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- የአዳማ ///ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022- 111-84-29 እና 022-211-89-25 እንዲሁም የአዋሳ ///ቤት ስልክ ቁጥር 046-212-53- 96 ወይም 046–212-65-95 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት

 

Save Tender