የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ለ2018 ዓ.ም ክልል አቀፍ 6ኛና 8ኛ ክፍል ፈተና አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እና የ147A የፕሪንተር ቀለም እና የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ በጀት የአብክመ ትምህርት ቢሮ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ በድጋሚ የወጣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ለ2018 ዓ.ም ክልል አቀፍ 6ኛና 8ኛ ክፍል ፈተና አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እና የ147A የፕሪንተር ቀለም እና የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ በጀት የአብክመ ትምህርት ቢሮ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ በድጋሚ የወጣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ፣ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች/ላፕቶፕ ኮምፒውተር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/፣ ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ዲጅታል ካሜራ 3000 /ሶስት ሺህ ብር/፣ ኤልሲዲ ፕሮጀክተር 3000 /ሶስት ሺህ/ እና ፍላሽ ባለ64 ጂቪ 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እና የኤሌክትሮኒክስ ስካነር ብር 50,000፣ ፕሪንተር ብር 10,000.00፣ ዲስክቶፕ ኮምፒውተር ብር 50,000.00፣ ኤልሲዲ ፕሮጀክተር ብር 3000 እና የ147A የፕሪንተር ቀለም ብር 50,000.00 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮ ህጋዊ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ስትመጡ በቢሮው አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቁጥር 1000012857253 ወይም አባይ ባንክ ቁጥር 2012116113625016 ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ የምትወስዱ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67/0583203999/በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
