አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/ግ/ማህበር በሚያስመጣቸው የግብርና መካናይዜሽን እቃዎች ዙሪያ ለዘመናዊ ግብርና ስላለቸው አስተዋፅኦዎች እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር ስላለው አዎንታዊ ተግባር በተጨማሪም ኩባንያችን ከዘመናዊ ግብርና ጋር በተያያዘ ስላለው አላማ እና ግብ ዙሪያ የ30 ደቂታ ዶክመንተሪ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላችሁን የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ቢያንስ 5 (አምስት) ዓመት ፕሮዳክሽን ልምድ ያለው
- የኩባንያ፣ የኢንዱስትሪ፣ የንግድ ወይም የልማት ዶክመንታሪ ስራ ልምድ ያለው
- የተሟላ የፊልም መሳሪያዎች (4K/HD Camera, Drone, Lighting, Sound)
- የPost-Production ችሎት (Editing, Color Grading, Sound Design)
- ጠቅላላ የፕሮዳክሽን አባላት ያሉት ማለትም
- ዳይሬክተር
- የካሜራ ሰራተኞች
- የኤዲቲንግ እና ሳውንድ ባለሙያዎች
- ስክሪፕት ማዘጋጀት የሚችል
- ቴክኒካል ፐሮፖዛል (Technical Proposal)
- ፋይናንስ ፕሮፖዛል (Financial Proposal) አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል
ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6፡30 ሰዓት ጨምሮ ነው።
የመጫረቻ ሰነዱ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ ነው።
የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ሟሟላት የሚጠበቅባቸውን ዝርዝር መስፈርቶች እና ሌሎች ዝርዝር ማብራሪያዎችን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመመልከት አሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0910048884 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር