በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የመረጃ ማዕከል አቅም ማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING) ማለትም፡ ዕከሉን ለማሳደግ የሚውሉ እቃዎችን የማቅረብ፣ የኢንስታሌሽን፣ ማይግሬሽን፣ ኮንፊገሬሽን፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽን ስራዎችን መፈፀም ጨምሮ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በካፒታል በጀት ማሰራት ይፈልጋል።
የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር-አብክመ /ኢቱቢ/ግ/ጨ/04/2018
በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የመረጃ ማዕከል አቅም ማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING) ማለትም፡ ዕከሉን ለማሳደግ የሚውሉ እቃዎችን የማቅረብ፣ የኢንስታሌሽን፣ ማይግሬሽን፣ ኮንፊገሬሽን፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽን ስራዎችን መፈፀም ጨምሮ በብሄራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በካፒታል በጀት ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉለት ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጠየቁ እቃዎችን በማቅረብ የኢንስታሌሽን፣ ኮንፊገሬሽን፣ ማይግሬሽን፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽን ስራዎች መስራት እና ሙያዊ ስልጠናዎችን መስጠት የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ እያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚሰሩ የመረጃ ማዕከል ማሳደግና ማዘመን (ኢንስታሌሽን፣ ኮንፊገሬሽን፣ ማይግሬሽን፣ ቴስቲንግ እና ኮሚሽን ስራዎችን ጨምሮ) እና የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 20 በማምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዳታ ማዕከል አቅም ማሳደግ (DATA CENTER UPGRADING) ስራ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን የንግድ ፈቃድ ሰነድ/ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ አንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ በሌላ ፖስታ ለየብቻ በታሸገ ሁለት ፖስታዎች በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ30ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው የሚለየው በሎት (ምድብ) ይሆናል።
- ተጫራቾች በቴክኒካል ሰነዳቸውም ሆነ በፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ማህተም ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583206856 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
ባህርዳር
