የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውል የታሸገ ውሃ እና የምግብ ቤት መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎችን ለዋና መ/ቤት እና ለደብረዘይት የስልጠና ማዕከል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 010/18
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውል የታሸገ ውሃ እና የምግብ ቤት መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎችን ለዋና መ/ቤት እና ለደብረዘይት የስልጠና ማዕከል የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚወዳደሩ
የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (ሁለት መቶ ብር) አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመከፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ብር በሲፒአ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ህጋዊ ሰነዶች ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ይህ የጨረታ ደብዳቤ ወጪ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደ አስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598/0118-69-4931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
