የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሕትመት ውጤቶች እንዲሁም የኪነ ጥበብ ውጤቶች /ለሚዲያ ግብዓት የሚጠቀምባቸውን/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት፡-
· የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
· የሕትመት ውጤቶች እንዲሁም
· የኪነ ጥበብ ውጤቶች /ለሚዲያ ግብዓት የሚጠቀምባቸውን/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡ፣ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ለሥራው በቂ ልምድና አቅም ያላቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለግዥ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሲዳማ ብ/ክ/መ/ሥነ-መግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 20 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሠነድ ጋር በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘውትር በሥራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት ይችላሉ።
5. የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ5፡30 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሥርዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
6. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· ለተጨማሪ መረጃ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን ስልክ ቁጥር፡- 046 212 7634 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
የሲዳማ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
