የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት የእርሻ ማሸነሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች (Farm Machinery Spare parts) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OSE/
NCB/015/2018
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት፡-
የእርሻ ማሸነሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች (Farm Machinery Spare parts) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
4. የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ16 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ17ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2፡30- 8:00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፤
ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11:30 ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ-
ስ.ቁ 011-416 03 09/011-466-25-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
