በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች፣ የጽዳት ዘርፍ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች፣ ጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 17/2018
በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች፣ የጽዳት ዘርፍ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ስፔርፓርት ዘርፍ እቃዎች፣ ጌጣጌጥ ዘርፍ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2018 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. በጨረታው ሽያጭ ሥርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ (የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር እያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ-ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ለሳተፍ ይችላል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ፣ በተራ ቁጥር 1 ከተገለጹት እና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና ፈርማ በግልጽ በመጻፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን 07/05/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
5. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ራሱን ከውድድር ውጭ ማድረግ አይቻልም፡፡
6. ለግልጽ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 07/5/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ሰዓት ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጥር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 07/05/2018 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ |
በ07/05/2018 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ 3፡50 ሰዓት ይከፈታል |
10. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች አርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።
11. ምድብ ለወጣላቸው ግልፅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የአጠቃላይ እቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡
12. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
13. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
14. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ የመረከብ እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡
15. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመሥሪያ ቤቱ ግቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
16. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
17. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተደደር የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
