የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የጽዳት ማሽኖች (Cleanining Machinaries:-Manual Road Sweepers, Pressure washers, Hot water high pressure cleaner, Blower Machine etc.) ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nomminees PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/ICB/22/18
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የጽዳት ማሽኖች (Cleanining Machinaries:-Manual Road Sweepers, Pressure washers, Hot water high pressure cleaner, Blower Machine etc.) ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል።
በዚህም የጽዳት ማሽኖች (Cleanining Machinaries) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በሀገር ዓቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደስ የንግድ ፈቃድ፤ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የምዝገባ ሰርተፍኬት የመሳሰሉትን ሰነዶች በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7:00-11:00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ የጽዳት ማሽኖች (Cleanining Machinaries) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
