ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የ BEARING (ኩሽኔታ) ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EAC 019
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. ማህበር የBEARING (ኩሽኔታ) ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጥር 7 ቀን 2018 ዓ. ም ጀምሮ እስከ ጥር 14 ቀን 2018 ዓ. ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 11:00 ድረስ ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. ማ ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
· አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
· አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
· ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
· በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የBEARING (ኩሽኔታ) ዕቃዎች ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.PO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ተፈጻሚ ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 667 6204 ፋክስ ቁጥር 011 673 2006 መጠቀም ይችላሉ።
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ. ማህበር
