የአስተዳደር ቢሮ እና ለሱቅ የሚሆኑ ክፍት ቦታዎች ጥናት ጨረታ የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር /በአሰራቸው ሕንፃዎች ላይ ለአስተዳደር የሚሆኑ ቢሮዎችን በዘመናዊ መልኩ ለማሰራትና የሕንፃውን የተለያዩ ክፍት ቦታዎች ለሱቅ አገልግሎት እንዲመቹ አጥንቶ የሚያቀርብ ባለሙያ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን ለማስጠናት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአስተዳደር ቢሮ እና ለሱቅ የሚሆኑ ክፍት ቦታዎች ጥናት ጨረታ የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር /በአሰራቸው ሕንፃዎች ላይ ለአስተዳደር የሚሆኑ ቢሮዎችን በዘመናዊ መልኩ ለማሰራትና የሕንፃውን የተለያዩ ክፍት ቦታዎች ለሱቅ አገልግሎት እንዲመቹ አጥንቶ የሚያቀርብ ባለሙያ በጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን ለማስጠናት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በመስኩ ልምድ ያላችሁ የህንፃ ምህንድስና ዲዘይን (Architectural design) ሙያተኞች በአካል በመገኘት ሕንፃውን አይታችህ መታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1. በዘርፋ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TI Number) ፣
3. ለሚከፈለው ከፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፣
4. በተመሳሳይ ሥራ የሰራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፣ ከላይ የተጠቀሱትን መሰፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (በአስር) የስራ ቀናት የምታጠኑበትን የሥራ ዋጋና አስፈላጊ ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ አክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት ትችላላችሁ።
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን አስረኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን አ/ማህበሩ ለተወዳዳሪዎች በስልክ ያሳውቃል።
6. የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀ በ2 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል። ይህ ካልሆነ ግን ስራውን በራሱ ፈቃድ እንደተወ ይቆጠራል።
ማሳሰቢያ፡-
· ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አጠና ተራ ከቴሌው ጀርባ ባለው የአ/ማህበሩ የገበያ ማዕከል ሕንፃ ቁጥር 2 አራተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 4
· ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-12-05-47-92 /09-32-08-03-77
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር
