Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 681 17 92
  • Website
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-01-30 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Firewood , Merchandise

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች የምግብ እህል፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት ለስድስት ወር ማለትም ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች የምግብ እህል፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት ለስድስት ወር ማለትም ከየካቲት 1 ቀን 2018 / ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 / በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያስታውቃል።

1.     በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ማስረጃ ያላቸውና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ መሆኑን።

2.     የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የተጨማሪ ዕሴት ታከስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ በብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ /ቤቱ የአዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች ሕጋዊ የምግብ እህል፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ፣ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት ለእያንዳንዱ የንግድ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ያላቸው።

5.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6.     ማንኛውም ተጫራች ፖስታውን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመምሪያው ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 08/05/2018 / ጀምሮ እስከ 22/05/2018 / ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 830 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና ጨረታው በዚሁ እለት 22/05/2018 / ከቀኑ 830 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 900 ሰዓት በማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7.     አሸናፊው በየወሩ እንደ ሕግ ታራሚዎች ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምር ሊቀንስ የሚችል ሲሆን እንዲቀርብ መምሪያው በሚገልፀው መጠን በየወሩ የሚቀርብ መሆኑን እና አሸናፊ ተጫራ ያሸነፉባቸውን በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

8.     የውድድሩ ሁኔታ በተናጠል በየዘርፉ በነጠላ የሚወዳደሩ መሆኑን እና ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሠረት ይከፈታል።

9.     ለበለጠ መረጃ ካስፈለገዎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 011 681 17 92 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

10. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን

 

Save Tender