ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ እየገነባ ለሚገኘው ለዋንዛየ ሎጅ ግንባታ ፕሮጀክት ceramic and porceilein በጨረታ ቁጥር 31/2018 ህጋዊና ብቃች ያላቸውን ፋብሪካዎች እና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2018
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውል ይዞ እየገነባ ለሚገኘው ለዋንዛየ ሎጅ ግንባታ ፕሮጀክት ceramic and porceilein በጨረታ ቁጥር 31/2018 ህጋዊና ብቃች ያላቸውን ፋብሪካዎች እና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ፈቃድ ለማደስ ግብር ስለመክፈላቸው የሚሰጥ ማስረጃ ያለው ያላት፤ ጨረታ ለመካፈል የሚያስችል ሰርተፊኬት ማቅርብ የሚችሉ፤ አቅርቦት እና ገጠማ ሥራ ከዚህ በፊት ለመስራታቸው ህጋዊ ከሆነ ተቋም የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሰ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም /unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
3. የጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራከሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ባህር ዳር ዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 የግን/ግብ/ግዥ እና አቅርቦት ኬዝ ቲም ቢሮ ክፍል ነው።
5. ውድድሩ በሎት /በጥቅል/ ዋጋ የሚታይ ይሆናል፤ ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር ባህርዳር 0582180538/09180106 17/0918164393 አዲስ አበባ:- 011-126-5652/5145/0912085639
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
