የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ በድርጅቱ የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተሰያዩ ያገለገሉ ንብረቶች የግልፅ
የጨረታሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ DIS/01/2018 ቁጥር
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ በድርጅቱ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ፤በሚሌ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል እና በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል አገልግለው የተመለሱ ንብረቶችን ማለትም በድርጅቱ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅርንጫፍ እና በሚሌ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጥገና ማዕከል የሚገኙ የከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጎማዎችን እና አገልግለው የተመለሱ የመኪና ባትሪዎችን እንዲሁም በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል አገልግለው የተመለሱ የወደብ መገልገያ ማሽነሪ ጎማዎችን፤ በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ የተነቀሉ ቴምበርድ መስታወቶችን፤ በቃሊቲ የሚገኙ የተነቀሉ ኮርኒሶችን፤ የተነቀሉ የኤሌክትሪከ ማቀፊያዎች፤ የተነቀሉ አልሙኒየም በሮችን፤ የተነቀሉ የእንጨት በሮችን፤ የተላቀቁ የእንጨት ሼልፎችን፤ ንቃይ ሴራሚኮች፤ ንቃይ ግራናይቶችን እና ንቃይ መጋረጃዎች ቁርጥራጭአልሙኒየሞችን እና ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታ ሂደቱ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ
1. የንግድ ምዝገባ፤ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
2. ያገለገሉ ጎማዎች እና ባትሪዎች ጨረታ ላይ መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶች ከአካባቢ ጥበቃ አኳያ በዘርፉ ለተሰማሩ እና ከሚመለከተው የአካባቢ ጥበቃ ወይም ከሚመለከተው የከተማ አስተዳደር/ክልል አካባቢን ሳይበከል መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ስለመሆኑ ፍቃድ ያለው ወይም የፅሁፍ የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
3. በተጨማሪም በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከቱትን አስገዳጅ ዝርዝርመመዘኛዎችን ማሟላት የሚችል ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2018ዓ.ም ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡ oo ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ብቻ የማይመለስ ብር1000.00 (አንድ ሺህ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመከፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል፡፡
ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ንብረቶቹን በዋናው መስሪያ ቤት፤ በቃሊቲ ትራኪንግ፤ በቃሊቲ መጋዘን፤ በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል እና በሚሌ የጥገና ማዕከል ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ፡፡
ጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ረቡዕ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2018ዓ.ም ከ8፡00 ሰዓት በፊት በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባርበተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ወይም በኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549304/0906329086 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡`
የኢትዮጵያ የባህር ተራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
