Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara National Regional State Education Bureau (የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ)
  • Address ባህር ዳር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-2-26-62-67
  • Websitehttps://anrseb.gov.et/
  • Deadline02 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-02-02 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ 2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት አመታዊ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ 2018 . በመደበኛ በጀት አመታዊ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1.     በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3.     የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6.     የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግሎጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ዓመታዊ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃ ማቅረብ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ግዥ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8.     የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡

9.     ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

11. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67 / 058 320 99 39 /በመደወል ማግኘት ይቻላል።

12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender