Tender Detail

Tender Details

  • Company ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen Fuer Menschen)
  • Address ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 471 42 91
  • Websitehttps://en.menschenfuermenschen.at/
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-01-30 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Plastic Raw Materials And Products , Cleaning And Janitorial Equipment

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen Fuer Menschen Foundation) ከዚህ በታች የተገለጹትን የምግብና የንጽህና እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት (Menschen Fuer Menschen Foundation) ከዚህ በታች የተገለጹትን የምግብና የንጽህና እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1.    አንደኛ ደረጃ የስንዴ ዱቄት - 1125 ኩንታል ደብረ ብርሐን ከተማ ድረስ ትራንስፖርት ጨምሮ እና ሳይጨምር። የስንዴ ዱቄት መያዥያ ከረጢት (ማዳበሪያ) የድርጅቱ ሎጐና አጭር ፅሁፍ ሊኖረው ይገባል።

2.     ፈሳሸ የምግብ ዘይት ባለ አምስት ሊትር ጠቅላላው 22486 ሊትር ደብረ ብርሐን ከተማ ድረስ ትራንስፖርት ጨምሮ እና ሳይጨምር።

3.     የልብስ ማጠቢያ ሳሙና 250 ግራም የታሸገ ወይም መሸፈኛ ያለው ብዛቱ 11243 ለጨረታ የሚቀርበው ምርት በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ደረጃ የተሰጠው ሆኖ የምርቱ ደረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ መጠቀስ አለበት።

4.     የሕጻናት መጸዳጃ (POPO)- ብዛቱ 1650 የድርጅታችን ሎን ህትመት ባለው እና በሌለው፣ ዳን ያለው፣ ኤክስፖርት ስታንዳርድ ወይንም ኢፖርትድ ደረጃ ያለው።

5.     PlUMPY HP ብዛቱ 110CARTON ደብረ ብርሐን ከተማ ድረስ ትራንስፖርትን ጨምሮ።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-

1.     በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣

2.     የንግድ ምዝገባና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     የግብር ከፋይ ምዝገባ /Tin Number/ ማቅረብ የሚችሉ እና፤

4.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ /ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩከ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን የጨረታ ሰነድ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በመቅረብ በማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ገዝተው እንዲሳተፉ ይጋብዛል። የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

5.     ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ምርት በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ ከተሰጣቸው ተቋማት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ (የተጨማሪ እሴት ስን ጨምሮ) 2% ሲፒአ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

7.     ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን ካላሟሉ ከጨረታ ይሰረዛሉ።

8.     ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መጠቀም አለባቸው። ተጫራች የሚያቀርበው የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላስቀመጠው የእቃው አይነት እና/ ወይንም መስፈርት (Specification) መሆን አለበት።

9.     ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ .. በአንድ ፖስታ ሌሎች የተጠየቁ የንግድ ሰነዶችን በሌላ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው። ፖስታዎቹም የዋጋ ማቅረቢያ እና የንግድ ሰነዶች በሚል ተጽፎባቸው ይቀርባሉ።

10. ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በትክል መሞላት አለበት፤ አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ የማይመለከተው ከሆነ በሚሰጡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ አይካተትም።

11. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ ጠቅላላ ድምር ወደ ጎንም ወደ ታችም ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው፣ የድምር ስህተት ቢኖር የተሰጠው ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።

12. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።

13. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ለእያንዳንዱ እቃ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል። በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለ በአቅራቢው መፈረማ አለበት።

14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ ቀናት ይቆይና በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና /ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 5 ቀይ አፈር አካባቢ በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል። አስረኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ በዓል ላይ ከዋለ የጨረታ መክፈቻው ቀን በቀጣይ የስራ ቀን ይሆናል።

15. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ነገር ግን ጥራቱ በድርጅቱ ታይቶ ተቀባይነት ካላገኘ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፣ ይህንን ባያደርግ ግን እቃውን ማቅረብ እንዳልቻለ ይቆጠራል፤ የአስያዘው CPO ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።

16. አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት። ይህንን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም አይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም። /ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም።

17. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በድርጅቱ የግዥ መመሪያ እና በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።

18. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ Menschen fur Menschen ስም አዘጋጅተው በፖስታ በማሸግ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

19. የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።

20. ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

21. ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም።

22. በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በከፊልም ሆነ በሙሉ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

23. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

24. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ የተወዳደሩበትን ምርት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

 

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 471 42 91 / 011 471 43 58 በስራ ሰዓት ደውሎ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

 

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት

(Menschen Fuer Menschen)

Save Tender