የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ሞተር እና ትራንስሚሽን በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሞተሮች እና ትራንስሚሽን ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ገመኮኤ 03/20
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ሞተር እና ትራንስሚሽን በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታውን ማስረጀዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚዝዙት የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ሞተር እና ትራንስሚሽን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ኤጀንሲው ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ደረሰኝ በማስቆረጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን 10/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 25/06/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠርመንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original acd Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት አየር ላይ ከዋለበት/ቀን 14/05/2018 ጀምሮ እስከ ቀን 29/05//2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጭን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ አፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ በቀን 29/05/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ግዥ ኦፊሰር ቢሮ 08:30 ኤጀንሲው አዳራሽ ይከፈታል።
11. ጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
12. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር-08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር -058-222-1115/058-320-7769 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
14. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
ባህር ዳር
