የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥጥ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የማሽንና ተሽከርካሪ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ገመኮኤ 04/2018
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥጥ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
1. በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN/ ያላቸው፣
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን (ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺ ብር/ በኤጀንሲው ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197968 ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ አርጅናል በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ደረሰኝ በማስቆረጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ14/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 13/06/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 14/05/2018 ጀምሮ እስከ ቀን 13/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጭን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ በቀን 13/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 8፡30 ወይም ኤጀንሲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
12. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር-08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር - 058-222-1115/058-320-7769 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
14. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
ባህር ዳር
