የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሰ.ቁ ኢት 4-21979 አይቬኮ የነዳጅ ቦቴ መኪና አገልግሎት የሚውል አጠቃላይ የሞተር ሲስተም ዕድሳት የጋራዥ ጥገና አገልግሎት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 08/2017
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሰ.ቁ ኢት 4-21979 አይቬኮ የነዳጅ ቦቴ መኪና አገልግሎት የሚውል አጠቃላይ የሞተር ሲስተም ዕድሳት የጋራዥ ጥገና አገልግሎት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የድጋፍ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የግ/ን/አስ/ኬዝ ቲም የቢሮ ቁጥር መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. የጨረታው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ሰላሳ /30/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ነው።
5. አቅራቢዎች ጨረታውን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው መሠረት አቅራቢው በፈለገው በአንዱ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ወጭ በኢንሹራንስ ዋስትና መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
ግ/ን/አስ/ኬዝ ቲም
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
ስልክ ቁጥር 046-13-15-008/0923690085
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
