የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 20/2018 በተለያዩ ጊዜያት ለሚያካሂዳቸው ውድድሮች ለሚጠቀምበት የቪዲዮ እና ፎቶ ካሜራ ሌንስ ግዥ በተያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 20/2018 በተለያዩ ጊዜያት ለሚያካሂዳቸው ውድድሮች ለሚጠቀምበት የቪዲዮ እና ፎቶ ካሜራ ሌንስ ግዥ በተያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደስ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽነ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 8፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፋክስ- 0116-45-08-79 ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
