Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ የአካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0901465288
  • Website
  • Deadline16 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-02-16 00:00:00
  • Categories Wood And Wood Working , Forest And Tree Sales

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተ/ጽ/ቤት በ07 ቀበሌ ገደሮ ልዩ ስሙ ስንጥር እና ባሕር ገንዳ ከሚባል ቦታ የሚገኘውን የባሕርዛፍ እና ጽድ የለማ የማኅበረሰብ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፊልጋል።


የደን ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን በወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ //ቤት 07 ቀበሌ ገደሮ ልዩ ስሙ ስንጥር እና ባሕር ገንዳ ከሚባል ቦታ የሚገኘውን የባሕርዛፍ እና ጽድ የለማ የማኅበረሰብ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፊልጋል።

1.     ለጨረታው የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል ለተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 ቀናት ማየት ይችላል

2.     የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው /ቤት በመገኘት ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ ብቻ ከፍሎ በሥራ ቀናት ወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ /ቤት መግዛት ይችላል።

3.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን አይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዥያ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ለእያንዳንዱ የደን ዓይነት እና ኮምፓርትመንት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4.     ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉት የእያንዳንዱን የደን ዓይነት እና ኮምፓርትመንት ወይም የሁሉንም ከፍልፋይ የሚገዙበትን ዋጋ ከስማቸውና ከአድራሻቸው ጋር በተናጠል ወይም ንድ ላይ በፖስታ በማሸግ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ /ቤት የማኅበረሰብ ደን ጨረታ ተብሎ በጉልህ ከተፃፈበት በኋላ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 20ኛው ቀን 400 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     የጨረታው ተወዳዳሪ የፈለገውን ኮምርትመንት አንድና ከአንድ በላይ ወይም ሁሉንም ኮምፓርትመንቶች ዋጋ መሙላት ይችላል፡፡

6.     የጨረታው ውድድር በኮምፓርትመንቱ በሎት ድምር ስለሆነ የባሕርዛፍና የጽድ ዋጋ መሞላት ሲኖርበት የአንዱ ዋጋ ብቻ መሙላት ከጨ ውጭ ያደርጋል።

7.     ተጫራቹ ጨረታውን ባሸነፈበት ዋጋ ለገቢዎች /ቤት 13% የሮያሊቲ ፍያ የመፈል ግዴታ አለበት፡፡

8.     ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር 20ኛው ቀን 400 ሰዓት ላይ ጨረታው ይዘጋል፤ በዚያው ዕለት 20ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተኙበት 430 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሑድ ወይም በዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይፈፀማል፡፡

9.     ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር፡- 0901465288/0957887630 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

10. /ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ የአካባቢና ደን ጥበቃ //ቤት

Save Tender