ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
በድጋሚ ጨረታ የሚወጡ የእቃ የአገልግሎት ግዥ
· ሎት 1 ሮል ወረቀት 80×60 ግዥ
· ሎት 2 ተቆልቶ የተፈጨ ቡና አቅርቦት ግዥ
· ሉት 3 አይብ አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና 2 የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ እና ለሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው።
11. የጨረታ ሂደቱ የቴከኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 ቴክኒካል ሠነድ ግምገማና የናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) እንደዚሁም ለሎት 2 ድርጅታዊ ብቃትና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት 60% እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት 40% ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ሠነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡
የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 5 53 07 67/011 5 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
