የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮችን ባሉበት ሁኔታ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/006/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮችን ባሉበት ሁኔታ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
የተቃጠሉ ትራንስፎርመሮች -25ኬቪኤ -200ኬቪኤ -50ኬቪኤ -315ኬቪኤ 100ኬቪኤ 800ኬቪኤ
|
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
|
በቁጥር |
36 |
67,151.78
|
የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥርእና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር(1000254843017 EEU Ambo District Connection Fee) የማይመለስ ብር 600/ስድስት መቶ/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት አምቦ ከተማ የዱሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ህንፃ ላይየቢሮ ቁጥር -14 2ኛ ፎቅ አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት አምቦ ከተማ የዱሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ህንፃ ላይ የቢሮ ቁጥር -14- 2ኛ ፎቅ አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።
8. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-2-60-97-77ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
