Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ከመድሃኒዓለም ት/ቤት ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መውረጃ 300 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-27-81-54
  • Website
  • Deadline26 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-02-26 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

2018 በጀት ዓመት 3 ዙር

 

የጨረታ ቁጥር፡-/////5///የጨ//003/18 ቀን፡- 03/06/2018 .

በአ///ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ /ቤት 2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር /ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

 

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

ከጠቅላላ ዋጋ የሚያሲዙት የብር መጠን

ሎት 1

ቋሚ ዕቃዎች/የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

30,000.00

 

በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

·        የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው።

·        የቫት/TIN NO/ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር በዌብ ሳይት ስለመመዝገባቸው መረጃ የምናይ መሆኑን

·        ተጫራቾች ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ለተወዳደራችሁበት አላቂ ዕቃ እና የልብስ ስፌት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባችኋል።

·        ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /cpo/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% በማስላት በማስያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህን ካላቀረቡ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።

·        ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማይመለስ ብር በካሽ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል በወረዳ 5 // ቤት 2ተኛ ፎቅ ወደ ቢሮው ሲገቡ በስተቀኝ በመግባት መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሠነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው።

·        በስራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ በራሳችሁ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለሚደረግ አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ ካደራጃችሁ አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ። በስራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ ከምታመርቱት ምርት ውጪ ባለ ዘርፍ እና ሰነድ ላይ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት cpo ማስያዝ ይኖርባችኋል።

·        ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን አካተው ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸ። ጨረታው 11ኛው የስራ ቀን 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ይከፈታል። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

·        ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሱን ማግለል አይቻልም።

·        የተጫራቾችን አድራሻ የሚገልፅ ሙሉ መረጃ ከሰነዱ ጋር መያያዝ አለበት።

·        መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

·        ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /cpo/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

·        ተጫራቾች የቢሮ መስተንግዶ ላይ የምትወዳደሩ የውሃና የቆሎ ሳምፕል ማቅረብ አለባችሁ።

·        ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ድርጅት ከጨረታ ውጭ ይሆናል።

·        አሸናፊ ተጫራች ድርጅት የአሸነፋችሁትን ዕቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ማቅረብ አለባችሁ።

·        አድራሻ፡-ከመድኃኒዓለም /ቤት ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መውረጃ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

·        ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-827-8154/

ማሳሰቢያ፡-በተጫረታችሁት ዕቃ ላይ ዋጋ ስታስገቡ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል መወዳደር የሚቻለው ንግድ ፈቃዱ ላይ በተሰጠው ስራ ዘርፍ በቻ ነው።

·        ተጫራቾች ያስገባችሁትን ሳምፕል በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለን አሽናፊና ተሸናፊ ከተለየ በኋላ 60/ስልሳ/የስራ ቀናት ውስጥ እንድትወስዱ እያሳሰብን በተቀመጠው ቀናቶች ውስጥ የማይወስድ ተጫራች ድርጅት /ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

·        ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዛችሁትን cpo ለውል ማስከበሪያ /ማዞር/ ማስያዝ አይቻልም።

·        ተጫራቾች ዋና የጨረታ ሰነድ ላይ ክፍል 2 እና ክፍል 6 በተጫራቾች የሚሞላውን ቅጽ መሙላት እና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መመለስ ይኖርባችኋል። ነገር ግን ክፍል 2 እና ክፍል 6 ላይ በተጫራቾች የሚሞላውን ቅፅ ያልሞላ ተጫራች እና የጨረታ ሰነዱን ካልመለሰ /ተመላሽ ካላደረገ/ ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟላ ተጫራች ጨረታው ውድቅ ይሆንበታል።

·        ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያም ሆነ ለውል ማስከበሪያ የምታስይዙት CPO ብቻ ነው። ከሲፒዮ ውጪ በቼክና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም። ካስያዛችሁም ከውድድር ውጪ ትሆናላችሁ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት

Save Tender