በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ነገሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጉራጌ ዞን ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ -
1. ሎት አንድ ------ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤
2. ሎት ሁለት ----- ፕላን ፕሎተር ማሽን፣
3. ሎት ሶስት ----- ባለ ሶስት እግር የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ትችላላችሁ።
1. ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ወይም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የታክስ ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
4. የአቅራቢት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. የግዢው መጠን ከብር 500,000/ አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ አይነት፣ የአምራቹን ስምና የተመረተበት ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
8. ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር ብቻ/፣ ለሎት 2 ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት 3 ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ከኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳዳቸው ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ ለጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
11. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡-
ሀ. ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች ከኦሪጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በሰም ማሸግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት/
ለ. ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ 16ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ያለበትን ሳጥን ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል።
13. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በውሉ መሠረት ዕቃዎቹን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
14. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊዎች ላቀረቡት እቃዎች የእጅ በእጅ ደረሰኝ ተጠቃሚ ከሆኑ ከገቢዎች የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል።
· ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 330 0112 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
· ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፤
· በጨረታው ሂደት ውስጥ ተሻሽሎ የወጣው አዲሱ የክልሉ የግዢ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልፃለን።
ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
