በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት CCTV ካሜራ ከነሙሉ ግብአቱ እና ከነገጠማው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 004/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት CCTV ካሜራ ከነሙሉ ግብአቱ እና ከነገጠማው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2-08 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ።
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3. አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. በዘርፉ በቂ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ማስፈርና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማና ማህተም በመምታት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከመወዳደሪያ ፖስታ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2-08 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 11 92 45 97
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
