በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆነው በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 0011/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆነው በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 0011/18 በ24/06/2018 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይል ግላሶች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ ስፔርፓርቶች፣ የእይታ ዕቃዎች/መነፅሮች፣ ኮስሞቲክስ እና መዋቢያዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ አርተፊሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ እወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1. የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
3. በሐራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገርግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድነኖ ግቢ ነው።
5. በሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፣
6. ተጫራቾች በሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፤
7. በሐራጅ ጨረታ ለወጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፡፡
8. የሐራጅ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያው መሰረት በዕለቱ ጠዋት 2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል፣
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደሩበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፣
11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለፁት ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ በባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
12. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይኖርባቸዋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
