Tender Detail

Tender Details

  • Company City Administration of Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 62 14 57
  • Websitehttps://addisconstructionwork.gov.et/
  • Deadline20 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-03-20 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Aluminium Supply and Work

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቁርጥራጭ አልሙኒየም እና ቁርጥራጭ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ቁርጥራጭ አልሙኒየም እና ቁርጥራጭ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከላይ የቀረቡትን ዕቃዎች ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ግለሰቦች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 1100 እና ቅዳሜ እስከ 600 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራከሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

1.     ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁርጥራጭ አልሙኒየም፤ ቁርጥራጭ ብረቶች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመያዝ በአካል መመልከት ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች ለመረጡአቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10 ሺህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት (City Government OF Addis Ababa Construction Design, Building and Consultation Enterprise) ስም ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና /un conditional bid bond/ የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በትከከል በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በላዩ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻ በመጻፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ .. /VAT/ የማይጨምር ሲሆን የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዙት ዕቃ ከአሸነፉበት ዋጋ በተጨማሪ የእሴት ታክስ 15% የመፈል ግዴታ አለባቸው

5.     ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው ያሸነፉበትን ዋጋ በቅድሚያ በመፈል ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸበት ቀን አንስቶ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ሲኖርባቸው፤ ይህ ባይሆን ግን ድርጅቱ ጨረታውን ሰርዞ ለማስከበሪያነት የተያዘውን ገንዘብ የሚወርስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

6.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 500 በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ላይ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

 

የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ

ስልክ ቁጥር 0946463816/0912085572

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት

Save Tender