በአብክመ ጤና ቢሮ የአማራ ሜዲካል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከሉ ቅርንጫፎች በባሕር ዳር እና በደሴ የሚገኙ ሲሆን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ማለትም መለዋወጫዎችን መሳሪያዎች ግዥ እና ለጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን ነጋዴው (አሸናፊው) እቃውን በማሟላት አጠቃላይ ጥገና እና ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ጤና ቢሮ የአማራ ሜዲካል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከሉ ቅርንጫፎች በባሕር ዳር እና በደሴ የሚገኙ ሲሆን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን ማለትም AirSep oxygen generator Rix booster and Air compressor መለዋወጫዎችን መሳሪያዎች ግዥ እና kaeser air compressor B+and C level ለጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን ንጋዴው (አሸናፈው) እቃውን በማሟላት አጠቃላይ ጥገና እና ግዥ ስለ ሚያስፈልጋቸው በዘርፉ የተሰማራችሁ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሞሉ ተጫራቾች እንዲትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት ተመዝጋቢ ከሆነ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200,000 ሁለት መቶ ሺህ/ብር በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. ቁ 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ውድድሩ በሙሉ ሰርቪስ ማድረግ ስለሆነ ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
6. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ በመውሰድ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሥራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 3% (ሶስት ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በማዕከሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና በየገጹ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተማ ፊርማ እና አድራሻው በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት 11፡30 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ማዕከሉ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 0415 / 058 320 1992 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 059 320 3088 መጠየቅና ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ጎን
የአማራ ሜዲካል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል
