Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የሚውሉ ለስብሰባ አዳራሽ የሚሆኑ የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና Wall-mounted Display Screen በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 005

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የሚውሉ ለስብሰባ አዳራሽ የሚሆኑ የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና Wall-mounted Display Screen በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የግዥ ቡድን በመቅረብመውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች በተስያዩ በሰም በታሸጉ ፖስታዎች

በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል። ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና Wall-mounted Display Screen በቀረበው ቴክኒካል እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ. ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት) ፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ: በስልክ ቁጥር 0111-57-24-97 በመደወል ወይም በአካል በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

Save Tender