በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በአን/ጠራ ወረዳ የኮቱ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ለሚያሰራው በከተማው የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ስራና የኮብልስቶን መንገድ ፕሮጀክት ማሽነሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
ግዥ በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በአን/ጠራ ወረዳ የኮቱ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ለሚያሰራው በከተማው የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ስራና የኮብልስቶን መንገድ ፕሮጀክት ማሽነሪዎች ማለትም፡-
CAT ግረደር CAT ኤክስካቫተር 2018፣ ሮሎ፣ ቦቲ 20,000 ሊትርና ሲኖትራክ ሰሌክት አፈር በሲኖ (ገረጋንቲ) ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደርየሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ የማሽነሪ ኪራይ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
3. በዘመኑ የታደሰ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት
4. የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
6. የምናከራየው የማሽነሪ አይነት ዝርዝር መግለጫ በተጨማሪ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ 1/100 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በጥሬ ገንዘብ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ።
9. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበት ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በአን/ጠራ ወረዳ ኮቱ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ፖስታውን እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ። በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ሰአት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
11. ተጫራቾች የማሽኖቹን ማጓጓዣ /የሎቤድ/፣ የሹፌርና የነዳጅ ወጭ በራሳቸው መቻል አለባቸው።
12. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና በላይ ሽያጭ ከተፈፀመ ዊዝ ሆሊዲግ ታክስ 3% ይቀንሳል።
13. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ቫትን የማይጨምር መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
14. ማሽኑ ሲወጣና ሲገባ በአስፓልት ከአዲስ አበባ 96 ኪ/ሜ ሲሆን ከደብረብርሃን አስፓልት 46 ኪ/ሜ ነው።
15. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ማዘጋጃ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
16. በዘመኑ የታደሰ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
ማሳሰቢያ፡- የዋጋ ዝርዝር ሲሞላ የነዳጅ፣ የሹፌርና የሎቤድ ዋጋ አብሮ ታስቦ መኖር አለበት፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 09 73 17 33 09 ወይም 09 13 01 10 63 ይደውሉ፡፡
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በአን/ጠራ ወረዳ የኮቱ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
