Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 098288 2826
  • Website
  • Deadline18 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2026-03-18 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለሞዴል የቅድመ አንደኛ መማሪያ ከፍሎች ማደራጃ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች እና ልዩ ልዩ የፅህፈት መሳሪያዎች መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ከ ችልደርን ኢን ክሮሰፋዬር /CiC/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 9 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ "Pathway to learning an integrated school Readiness Program for early learners " የሚል ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ ለነዚህ በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ግብአቶችን ለመግዛት አቅዷል። በመሆኑም የሚከተሉትን ቁሳቁሶች ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የሚገዙት ቁሳቁሶችም የሚከተሉት ናቸው።

ለሞዴል የቅድመ አንደኛ መማሪያ ከፍሎች ማደራጃ የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች

ልዩ ልዩ የፅህፈት መሳሪያዎች (የእቃዎቹን ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያገኙታል)

 ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1.     ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2.     የቲን ምዝገባ ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣

4.     ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ፣

5.     ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፦

አድራሻ: ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/

አዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ

ስልክ፦ 09 82 88 28 26

1.     አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግብዓት ከማቅረባቸው በፊት ሳምፕል ማሳየት ይኖርባችኋል።

2.     ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል። በትክክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደረጎ ይቆጠራል።

3.     ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/

Save Tender