የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል በሎት አንድ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ በሎት ሁለት ቋሚ ዕቃዎች/ ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች/፣ በሎት ሦስት አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም በሎት አራት ለጋራዥ አገልግሎት የሚውሉ የወርክ ሾፕ ዕቃዎች ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 10/2018
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል በሎት አንድ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ በሎት ሁለት ቋሚ ዕቃዎች/ ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች/፣ በሎት ሦስት አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም በሎት አራት ለጋራዥ አገልግሎት የሚውሉ የወርክ ሾፕ ዕቃዎች ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ከሃምሳ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. የጨረታው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ሰላሳ ለ30/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
4. የጨረታው አሸናፊ የሚወስነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ነው።
5. አቅራቢዎች ጨረታውን አንድ - ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ለዚህ ተግባር / በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች ለሎት አንድ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ እና / ለሎት ሁለት ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለሎት ሦስት ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ እና ለሎት አራት ደግሞ ብር 250,000.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው መሠረት አቅራቢው በፈለገው በአንዱ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ዋስትና መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
ስልክ ቁጥር 0461315012/0932708847,923690085
ደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
