Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል

ü የተሽከርካሪና ማሽነሪዎች ኪራይ

ü የተሽከርካሪና ማሸነሪ መለዋወጫ

ü የተሽከርካሪና ማሽነሪ ጎማ

ü የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት

ü የህንጻ መሳሪያ

ü ብሎኬት

ü አሸዋ ድንጋይና የተፈጨ ጠጠር

የቫይብሬተር ሆዝና ሚክሰር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በነጠላ ዋጋ ውድድር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የተሰጠ ወይም የታደሠ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡

2. የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% ከነቫቱ በባንከ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘ ተጫራች የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፤ የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

6. የመጫረቻ ሰነዱ /የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን /አርባ ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡

7. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ይሆናል፡፡

8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመከፈል

ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡

10.ማንኛውም ተጫራቾች ያቀረበው የጨረታ ሰነድ ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ የሌለው ወይም የጨረታ ማስከበሪያው የሚያንስ ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብ ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

11.ተጫራቾች ዋጋ መሙላት የሚችሉት መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙሊያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙሊያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን ከውድድር ውጭ የሚያደርግ ይሆናል።

12.በጨረታ በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖርአለበት፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከውድድርውጭ ያስደርጋል፤

13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

14.አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ/ተሽከርካሪ/ማሸነሪ/ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዣ፣ ማስጫኛ እና ማውረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

15.የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

16.በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

17.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 91 72/ 033 311 10 41/10 48/ 10 59 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤

አድራሻ ፡- ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት

የደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን

Save Tender