Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ በሀራጅ ጨረታ

ቁጥር 0012/2018

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ //ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መስረት፡-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 0012/08 17/07/2018 የተለያዩ አልባሳት ኤሌክትሮኒ እቃዎች ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይል ግላሶች እና ከቨሮች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ ስፔርርቶች፣ የእይታ ዕቃዎች መነፅሮች ኮስሞክስ እና መዋቢያዎች፣ ዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ አርትፍሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1.     የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል።

2.     ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።

3.     በሀረጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመፈል ሪሲት በመውሰድ ትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 130 እስከ ቀኑ 12 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ 2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገርግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ//ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

4.     ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድነኖ ግቢ ነው።

5.     ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

6.     ተጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን //ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

7.     በሀራጅ ጨረታ ለወጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባን (ንግድ ባን) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን //ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

8.     የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት 200 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ 400 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።

9.     በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ /ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።

12. የጉምሩክ ኮምሽን //ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ //ቤት

Save Tender