በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም በጀት ድጋፍ፣ የትራክተር ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የድጋሚ የወጣ ትራክተር ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 371/18
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም በጀት ድጋፍ፣ የትራክተር ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚታሸግበት ሰዓት |
ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
ትራክተር ከነ ማረሻ |
በቁጥር |
1 |
100,000 |
በ31ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ሰዓት ይከፈታል |
ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
በንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት መዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለት ተከታታይ ቀናት እስከ 30ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡበ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ወስጥ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና እንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ አዘጋጅቶ በማሸግና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ከቶ በማሸግ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮው ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል፡፡
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ማለትም 31ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
- ከአንድ በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- 046-131-0134 ይጠቀሙ።
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
