የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 29/2018 በተለያዩ ጊዜያት ለሚያካሂዳቸው ውድድሮች ላይ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ ለመያዝ እንዲያስችለን ብዛት ሶስት /3/ Samsung Galaxy S25 Ultra ግዥ በተያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቁጥር 29/2018 በተለያዩ ጊዜያት ለሚያካሂዳቸው ውድድሮች ላይ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ ለመያዝ እንዲያስችለን ብዛት ሶስት /3/ Samsung Galaxy S25 Ultra ግዥ በተያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሽገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 8፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ:- 0990-04-09-40/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፋክስ 0116-45-08-79
ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
