የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት ለከባድ እና ለቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ለሰርቪስ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል ጂፒኤስ (GPS) ከነገጠማ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ጂፒኤስ ከነገጠማው ግዥ ለመፈፀም በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/ 19B/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት ለከባድ እና ለቀላል ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ለሰርቪስ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል ጂፒኤስ (GPS) ከነገጠማ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ ማስረጃ ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ ቲን፣ የፍሊት ማናጅመንት ብቃት ማረጋገጫ እና በEGP የአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ ስለመሆኑ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ጉምሩክ ከባቡር መነሻ ፊት ለፊት በሚገኘው አዋሽ ባንክ በኩል ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ60 (ስልሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል። ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመከፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ +251911984467 @ +251910567578
ፋስክ 0114-421312
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
