አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ ለኩባንያው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈትና የፅዳት ዕቃዎችን፣ ቨርቲካል የቢሮ መጋረጃ እና ሎት 3 የተሽከርካሪ ጎማና ጌጣጌጦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 07/2018
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ ለኩባንያው አገልግሎት የሚውሉ፡
· ሎት 1 የተለያዩ የጽሕፈትና የፅዳት ዕቃዎችን
· ሎት 2 ቨርቲካል የቢሮ መጋረጃ
· ሎት 3 የተሽከርካሪ ጎማና ጌጣጌጦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለሎት 1 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር)፣ ለሎት 2 20,000 (ሃያ ሺ ብር) እና ለሎት 3 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ሕንፃ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ ኢማ ዋና መሥሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች ከኩባንያው ጋር ውል በመግባት አጓጉዘው በኩባንያው የንብረት ማከማቻ መጋዘን ገቢ ማድረግ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በቀን 14/8/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
7. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:-
ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ሕንጻ ጎን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-1-26-38-88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አዲስ የካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ሥራ አ.ማ
