Tender Detail

Tender Details

  • Company የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
  • Address , Phone: 0461800863
  • Website
  • Deadline30 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-04-30 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የኤሌትሮኒ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም

1.     በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸዉ መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና 2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስከርወረቀት ማቅረብ የሚችሉና eGP የተመዘገቡ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች፤ ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።

3.     የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ደት ቢሮ ይሆናል፡፡

4.     ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨሪታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።

5.     ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት 16ኛው ቀን ከቀኑ 400 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4:30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

6.     ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በታወቀ ባን የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7.     የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።

8.     የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የወይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ልማት መምሪያ

በለጠ መረጃ 0461800563 ደው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ልማት መምሪያ

Save Tender