Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 220 4516
  • Website
  • Deadline08 May 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2026-05-08 00:00:00
  • Categories Office And Home Furniture , Office Machines And Accessories , Office Equipment

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ የመገልገያ ቁሳቁሶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በሪስቶር ፕሮጀክት በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የእንስሳት ሃብት አገልግሎት መልሶ ማቋቋም ድጋፍ ለሦስት ዘር አምራቾች ማህበራት እና ለሦስት የእንስሳት መኖ ዘር አምራቾች ኢንተርፕራይዝ የተለያዩአይነት የመስሪያ ቁሳቁሶችን በሪስቶር ፕሮጀክት በጀት ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የመገልገያ ቁሳቁሶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታ ቁጥር እሀልማቢሮ 133/2018 የእንስሳት መኖ ዘር አምራች ማህበራት እና ኢንተርፕራይዝ የመገልገያ ቁሳቁስ ግዥ፣

የእቃው ዝርዝር

 

Ø  የኬሻ ጆንያ መስፊያ ማሽን

Ø  የመስፊያ ክር

Ø  የዘር መያዥያ ኬሻ ጆንያ ባለ50 ኪግ

Ø  የምድር ሚዛን

Ø  የሚዛን ድንጋይ ባለ 1 ኪግ እና ባለ 0.5ኪ. ግ

Ø  ናፕሳክ መርጫ

Ø  ማጭድ

Ø  ቾፐር

 

 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል

1.     በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2.     የሚገዙ ግብዓቶች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላለ።

3.     ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 103374.00 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 69 የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

5.     የመወዳደሪያ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል።

6.     ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና የዋጋ ማቅረቢያ/ፋይናሻል ፕሮፖዛል እያንዳንዱን ለየብቻው ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል፤

7.     ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ መታሸግ ያለባቸው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፣ የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናት፣ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በስንት ቀን ውስጥ እቃውን አጠቃሎ ማስረከብ ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ፤

8.     ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ጋር አብሮ በፖስታ ማሸግ ያለብዎት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ ነው።

9.     በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 4516 /058 220 6479 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

10.  ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይከፈታል፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።

11.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 058 220 4516 ወይንም 058 220 6479

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ

 

Save Tender