ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር የSolar Powered Backup Battery with Hybrid Inverter and Required Accessories ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EAC 029/2018
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር የSolar Powered Backup Battery with Hybrid Inverter and Required Accessories ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ከሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11፡00 ሰዓት ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
- አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ፡፡
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ እንዲሁም፡፡
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የSolar Powered Backup Battery with Hybrid Inverter and Required Accessories ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም ኮንዲሽናል ባንክ ጋራንት ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ በሮ ቁጥር 208 ሲሆን፤ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ከሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል፡፡
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 ደውለው መጠቀም ይችላሉ፡፡
8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር
