በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለAI (ሰው ሰራሽ እንስሳት ማዳቀል) ፕሮጀክት ቁሳቁሶችን ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት ለAI (ሰው ሰራሽ እንስሳት ማዳቀል) ፕሮጀክት ቁሳቁሶችን ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑ የቲን ሰርተፍኬት /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከዛ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ፈቀድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለጨረታ ዶክመንቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በሶዶ ግብርና ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ተከፍተው በሚገኘው አካውንት ቁጥር 1000018208443 በማስገባት አድቫይስ በመያዝ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግ/ከ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
3- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድርሻቸውን በመጥቅስ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግ/ክ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 41 ይከፈታል፡፡ 16ኛው የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
6- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ሰርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
7- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች እስከ ኮሌጁ ድረስ አቅርቦ ያስረክባል፡፡
8- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0465513984 መደወል ይቻላል፡፡
ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ
