Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
  • Address , Phone: 0582205849
  • Website
  • Deadline24 May 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-05-24 00:00:00
  • Categories Seed

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የተለያዩ የአትከልት ዘሮች ግዥ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የተለያዩ የአትከልት ዘሮች ግዥ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1.       በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።

2.       የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።

3.       የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብርበላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4.       ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5.       የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕለስቲክ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

6.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ  ብርበመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።

7.       ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ለሎት 01 ብር 100,000.00 /አንድ መቶ  ብርየጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditonal Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ/የመወዳዳሪያሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።

8.       ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16 ቀን ቅዳሜ  እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 400 ታሽጎ 430 ይከፈታል።

9.       /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.   በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849 / 058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

11.   ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።

12.   በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

 

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ

Save Tender