Tender Detail

Tender Details

  • Company የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን
  • Address ሐረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910415925
  • Website
  • Deadline19 May 2026, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-05-20 00:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን በሐረሪ ክልል በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ ለንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ እስከ በተዘረዘረው መሰረት በሐረሪ ክልል በተለያዩ አካባቢ የሚገኙ (1-ንደኛ መንገድ አሚር ኑር ፖሊስ ጣቢያ 2- ጤና ቢሮ ፊት ለፊት : 3- ቀላዳንባ እና 4- ማልቴዝ ጀርባ ) ለንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ የሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።


በመሆኑም፡-

1.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሚያዚያ 28/2018 / እለተ እሮብ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽ ቢሮ በቢሮ ቁጥር 34 ዘወትር በስራቀናት እና በስራ ሰአት መግዛት ይችላሉ።

2.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ለቦታዎቹ በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ ማወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አደርጎ ለጨረታው ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ስከ ግንቦት 11 እለተ ማክሰኞ 2018 . ከቀኑ 1100 ሰአት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3.     ጨረታው በቀን 11/9/2018 / ከቀኑ 1100 ተዘግቶ፤ በቀን 12/9/2018 . ከጠዋቱ 400 ዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አራተኛ ፎቅ ላይበሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት 5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80 በመቶ ነጥብ ሲኖረው የቅድሚያ ፍያ መጠን ደግሞ 20 በመቶ ነጥብ ይኖረዋል። የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሁለቱ ነጥቦች ድምር በሚገኝ ውጤት ይሆናል።

6.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድሚያ ከፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ለንግድ 20 በመቶ ማነስ የለበትም።

7.     የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በግልፅ በይፋ ከተገለፀ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ተመላሽ ይደረግላቸዋል

8.     ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።

9.     ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0919121917 ወይም 0910415925 ዘወትር በስራ ሰአት በመደወል ማግኘት ይችላሉ። የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ድህረ-ገፅ https://www.hararilanddev.gov.et ወይም ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ማግኘት ይችላሉ።


የሐረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለስልጣን

Save Tender