Tender Detail

Tender Details

  • Company የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline23 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-05-23 00:00:00
  • Categories Construction Machinery , Construction Vehicle

በአፈፃፀም ከሳሽ- ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአፈፃፀም ተከሳሽ- ፍሊንትስቴን ኢንጅነሪንግ መካከል ባለው የአፈፃጸም ክርክር ጉዳይ ዊል ሎደር ማሽን በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይጋብዛል።


የጨረታ ማስታወቂያ


አፈፃፀም ከሳሽ- ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአፈፃፀም ተከሳሽ- ፍሊንትስቴን ኢንጅነሪንግ መካከል ባለው የአፈፃጸም ክርክር ጉዳይ፤ በተከሳሽ ድርጅት ፍሊንትስቴን ኢንጅነሪንግ ወይም ባለቤት ፀደቀ ይሁኔ ወልዱ ስም የተመዘገበ ዊል ሎደር ማሽን አፈ/ተከሳሽ ስም የተመዘገበው በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሳይት ውስጥ የሚገኘው ማሽን በግልጽ ጨረታ በመነሻ ግምቱ ዋጋ ብር 1,160,651.40 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ስድስት መቶ አምሳ አንድ ብር ከአርባ ሳንቲም) ሆኖ ግንቦት 15 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 630 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በጨረታ እንዲሸጥ የአብ ጠቅላይ /ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት በመመደብ የአማራ ክልል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያም ፀጥታውን የሚያስከብር አንድ ሰው በመመደብ የጨረታው ስነ-ስርዓት በአግባቡ እንዲከናወን እንዲደረግ ሆኖ የአብክመ ጠቅላይ /ቤት ሐራጅ ባይም ጨራታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሳይት ውስጥ በመሆኑ ማሽኑን ለመግዛት መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከቦታው በመገኘት ምልከታ አድርጐ ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መጫረት መሳተፍ የሚቻል እና አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ለፍ/ቤቱ ሐራጅ ባይ በሲፒኦ የመክፈል ግዴታ ያለበት ሲሆን ጠቅላላ ዋጋውን በሃያ ቀናት ውስጥ ሲያጠናቅቅ ማሽኑን መረከብ የሚችል መሆኑን እንዲያውቁት የአብክመ ጠቅላይ /ቤት አዟል።


የአብክመ ጠቅላይ /ቤት

 

Save Tender