Tender Detail

Tender Details


   ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011፣ 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የመያዣ ንብረቶች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ   ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


                                                     ወጋገን ባንክ አ.ማ

                                           ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ማስታወቂያ

                                          ቁጥር፡ ወጋገን 024/2018

     ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011፣ 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የመያዣ ንብረቶች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ   ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

      የማይንቀሳቀስ ንብረት የሀራጅ ጨረታ ዝርዝር

 

ተቁ የተበዳሪው ስም ንብረት አስያዥ አበዳሪው ቅርንጫፍ የንብረቱ አድራሻ የቦታው

ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ጨረታው የሚከናወንበት ጊዜ
ከተማ/

ክልል

ክ/ከተማ/ ከተማ/ዞን ወረዳ/

ቀበሌ

ቀን ሰዓት
1 አቶ ነጋሲ ኪዳነ ተክለ

 

ተበዳሪዉ ሽረ

እንዳስላሴ

ትግራይ ሸረ

 

03 100 ካ/ሜትር 3633/

3310/08

መኖሪያ ቤት፣ (G+2) ግንባታው ሰባ አራት በመቶ (74%) ያለቀ 3,157,790.99 ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 – 6፡00 ሰዓት
2 አቶ ተኽላይ ብርሃነ አባይ ኪሮስ

በላይ

ዓድዋ ትግራይ ዓድዋ 01 375 ካ/ሜትር 1958/07 መኖሪያ ቤት፣ ግንባታው (ስልሳ አምስት በመቶ /65%/ ያለቀ 2,307,037.06  

ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም

 

ከጧቱ 3፡00 – 6፡00 ሰዓት

3 ገብረህይወት አባዲ(ኢትዮ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ) ተበዳሪዉ ቃሊቲ ትግራይ አድዋ 07 2500

ካ/ሜትር

290/96 የንግድ ህንፃ (G+8)                                 ሲኒማ እና ስቶር ያጠቃለለ፣ ግንባታው ሰባ አምሰት በመቶ (75%) የተጠናቀቀ 86,950,619.96

 

 

የተሽከርካሪ የሀራጅ ጨረታ ዝርዝር

 

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም ንብረት አስያዥ አበዳሪ

ቅርንጫፍ

የተሽከርካሪ            ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የሞተር ቁጥር        ዘመን የነዳጅ

አይነት

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ጨረታው የሚከናወንበት ቀን
ቀን ሰዓት
1

 

ዮቴክ ኮንስትራክ                                                 ሽን ኃ/የተ/የግ/

ማህበር

ተበዳሪው ድርጅት ጎፋ  

አውቶሞቢል

አአ-03-54277 SCP10-3146361 1SZ-0275268 1999 ቤንዚን 300,000.00 ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ

 

 

ማሳሰቢያ  

 

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በውስጥ መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  4. የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለእያንዳንዱ ንብረት የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡
  5. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ጨረታው የሚካሄደው፡ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ፡- ማለትም በመጀመሪያው ሰንጠረዥ ተ.ቁ.1 ላይ የሚገኘው ንብረት በባንኩ ሽሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ በተ.ቁ.2 እና 3 ላይ የተዘረዘሩት በባንኩ ዓድዋ ቅርንጫፍ እንዲሁም በሁለተኛው ሰንጠረዥ ላይ የተጠቀሰው ንብረት በባንኩ ዋ/መስሪያ ቤት ህንጻ 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
  8. ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
  9. ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
  10. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  11. ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ የሽሬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፡ 034-244-3685/ 034-244-4248 እና የዓድዋ ቅርንጫፍ፡ 034-771-4046/ 034-771-4043 መደወል ይችላሉ፡፡  
  12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ወጋገን ባንክ አ.ማ

 

 

Save Tender