Tender Detail

Tender Details


አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 11 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተ.ቁ
የተበዳሪው ስም
የመያዣ ሰጪው ስም
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት
የቦታው ስፋት በካ.ሜ
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን
የምዝገባ ሰዓት
የጨረታሰዓት
ጨረታው የወጣዉ
1
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ
ተበዳሪዉ
የመኖሪያ ቤት
350
ቦሌ12/2/3/10/20334/117118/02
አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12
40,522,271.95
ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም
4፡30-5፡30
5፡30-6፡00
ለመጀመሪያ ጊዜ
2
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ
ተበዳሪዉ
የመኖሪያ ቤት
105
AA000090701126
አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07
6,741,507.79
ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም
8፡30-9፡30
9፡30-10፡00
ለመጀመሪያ ጊዜ
3
አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ
ወ/ሮ እታየሁ አስታጥቄ
የመኖሪያ ቤት
105
AA000090701487
አዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07
7,227,177.21
ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም
8፡30-9፡30
9፡30-10፡00
ለመጀመሪያ ጊዜ
4
ሰሚክ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አቶ ሚካኤል ስብሆ
የመኖሪያ ቤት
72
AA000060808751
አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ሰሚት ሰንሻይን አፓርትመንት አከባቢ
15,620,076.60
ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም
4፡30-5፡30
5፡30-6፡00
ለመጀመሪያ ጊዜ
5
ፍራንኩን ኢት አዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አቶ ሊዮናርዶ ቨሎኔ
መጋዘን
3000
G/K/L/I/29/2000
ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ
9,425,851.72
ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም
8፡30-9፡30
9፡30-10፡00
ለመጀመሪያ ጊዜ

 

Save Tender