Tender Detail

Tender Details


 ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል  


ወጋገን ባንክ አ.ማ

 ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር፡ ወጋገን 022/2018

 ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል                        

ተቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ የንብረቱ አድራሻ የቦታው

ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር   የንብረቱ

ዓይነት/የይዞታው

  አገልግሎት                                                                                  

የጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታው የሚከናወንበት ቀን
ከተማ/

ክልል

ክ/ከተማ/ ከተማ/ዞን ወረዳ /ቀበሌ
1 ቴዎድሮስ ታደሠ እና አቢሲንያ የቄራ

አገልግሎት ኃላ/የተ/                   የግ/ማህበር

አቶ  ቴዎድሮስ ታደሰ በቅሎቤት አዲስ አበባ    የካ 13 1,012

ካ/ሜትር

AA000051308702 የንግድ ህንጻ

(B+G+6+ ቴራስ)

 

179,473,281.05

 

ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ

3፡00 6፡00 ሰዓት

 

 

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. ጨረታውን ላሸነፈ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ እንዲሁም ተጨማሪ የመያዣ ንብረት ለሚያቀርብ ተጫራች፤ ባንኩ በብድር መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  4. የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡
  5. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ጨረታው የሚካሄደው በወጋገን ባንክ ዋና መስርያ ቤት ህንጻ 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ይሆናል፡፡
  8. ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
  9. ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
  10. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  11. ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይችላሉ፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

                                ወጋገን ባንክ አ.ማ       

Save Tender